The Ethiopian News Agency dispatches text news, and audio and video stories about local and international events to media enterprises and the public.
#ethiopiannewsagency #ethiopiannews #dailynews #Daily_mereja #Mereja #fyp #foryoupage #ethiopia_today #Today's_News #todaysnews #abiy_ahimed #Adis_mereja #ኢዜአ #ዜና #ዜናስፖርት #ዜናቅምሻ #እለታዊ_መረጃዎች #የቀን_ዜና #የማታ_ዜና #adismereja #አዲስ_አበባ #ኢትዮጵያ #የኢትዮጵያ_ዜና #yeqen_merejawoch #football #ethiopiannews #Zena
Ethiopian News Agency (ENA)
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት ተመርቆ ለአገልግሎት የበቃው የእንጦጦ ፒኮክ የወንዝ ዳርቻ ልማት አካል የሆነው፣ ከቀጨኔ በአምባሳደርና በኢሬቻ እስከ ባምቢስ የተዘረጋው የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ዋና ዋና ውጤቶች፦
ከቀጨኔ በአምባሳደርና በኢሬቻ እስከ ባምቢስ የተዘረጋው ይህ ፕሮጀክት 351 ሄክታር ስፋትና 10 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍን ሲሆን፣ የተለያዩ ዘመናዊ መሠረተ ልማቶችንና የሕዝብ መገልገያዎችን አካትቷል።
✍️ የተፈጥሮና የአካባቢ ጥበቃ
የአፈርና የውሃ ጥበቃ፣ የወንዝ ማጽዳት፣ የጎርፍ መከላከል፣ የአረንጓዴ ስፍራዎችን ማስፋፋትና የገጽታ ማስዋብ ሥራዎች ተከናውነዋል።
✍️ ዘመናዊ የመንገድና የእግረኛ መሠረተ ልማት
• 16 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ፤
• 20 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መንገድ፤
• 22 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ፤
• 5 ኪሎ ሜትር የመሮጫ ትራክ፤
• 18 የተሽከርካሪ ድልድዮች፤
• 23 የእግረኛ ድልድዮች ተገንብተው፣ ነባሮቹም ታድሰዋል።
✍️ለስፖርት፣ ለመዝናኛና ለማኅበራዊ ትስስር የተዘጋጁ ስፍራዎች
ፕሮጀክቱ 12 የስፖርትና የጤና ማዕከላትን፣ ዘመናዊ የስፖርት ሜዳዎችን፣ ጂምናዚየሞችንና የፉትሳል ሜዳዎችን አካትቷል።
በተጨማሪም፦
• 21 የሕፃናት መጫወቻ ስፍራዎች፤
• 15 ፕላዛዎችና አምፊ ቲያትሮች፤
• 8 ፋውንቴኖችና የውሃ ትርዒት ማሳያዎች፤
• በተለያዩ አካባቢዎች የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶች ተገንብተዋል።
✍️ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴና የሥራ ዕድል ፈጠራ
የከተማችንን ኢኮኖሚ ለማሳደግ፣ የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የሥራ ዕድሎችን ለማስፋት 30 ካፌዎችና 185 ሱቆች ተዘጋጅተዋል። የባንክ አገልግሎቶችም ተካትተዋል።
በወንዝ ዳርቻው አካባቢ ለሚኖሩ ነዋሪዎች የኑሮና የአኗኗር ሁኔታን ታሳቢ ያደረገ የዕደ ጥበብ ምርቶች ማምረቻ፣ ማሳያና መሸጫ ማዕከል ተዘጋጅቷል። በተጨማሪም የግብርና ምርቶችን ለማቅረብና ለመሸጥ የሚያስችል ማዕከል ተካትቷል።
✍️የውሃ፣ የፍሳሽና የጎርፍ መውረጃ መሠረተ ልማት
የከተማ ዩቲሊቲዎችን ለማዘመንና የፍሳሽ አወጋገድ ሥርዓቱን ለማሻሻል፦
• 6 ኪሎ ሜትር የንጹሕ ውሃ መስመር፤
• 11 ኪሎ ሜትር የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር፤
• 12 ኪሎ ሜትር የጎርፍ መውረጃ መስመር፤
• 5 አነስተኛ ግድቦች፤
• 6 የውሃ ፍሰት መቆጣጠሪያ ግድቦች፤
• 3 የውሃ ማጣሪያ ማዕከላት ተገንብተዋል።
እነዚህ መሠረተ ልማቶች የውሃ ሀብታችንን ለመጠበቅ፣ የጎርፍ አደጋን ለመቀነስና የአካባቢውን ጤናማነት ለማሻሻል ወሳኝ ሚና ይኖራቸዋል።
✍️ ለዘላቂ ትራንስፖርትና ለአካባቢ ጥበቃ የተዘጋጁ መሠረተ ልማቶች
የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋምና ምቹ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎችን ለማስፋት 22 የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎችና 8 የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ ማዕከላት ተገንብተዋል። እነዚህ ማዕከላት በአንድ ጊዜ ከ100 በላይ መኪናዎችን ቻርጅ ለማድረግ ያስችላሉ።
✍️የከተማችንን ታሪክና ባህል የሚያስተዋውቁ መገለጫዎች
የወንዝ ዳርቻ ልማት ሙዚየምና “ወደ ምንጩ መመለስ (Back to Origin)” የተሰኘው ሐውልት የከተማችንን ታሪክ፣ ባህልና የተፈጥሮ ሀብት አስፈላጊነት የሚያስተዋውቁ ልዩ መገለጫዎች ናቸው።
የልማታችን ዓላማ የሰው ሕይወትን ማሻሻል ነው!
የዚህ ልማት ዓላማ ውብ ስፍራዎችን መገንባት ብቻ ሳይሆን፣ ለነዋሪው ጤናማ አካባቢ፣ የመዝናኛ አማራጮች፣ የኢኮኖሚ ዕድሎችና የተሻለ የኑሮ ሁኔታ መፍጠር ነው።
@EthiopianNewsAgency
15 hours ago | [YT] | 339
View 8 replies
Ethiopian News Agency (ENA)
የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሀገር ህልውና ምሶሶ ነው - ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ)፦ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሀገር ህልውና ምሶሶ ነው ሲሉ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ገለጹ።
ዓባይ የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጸጋ ቀይ ባህርም ፈጣሪ ለኢትዮጵያ ያበጀው ባህር መሆኑን ገልጸዋል።
119ኛው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቀን የድል ሰራዊት በሚል መሪ ሀሳብ በጦር ኃይሎች ጠቅላይ መምሪያ ተከብሯል።
ቀኑ የመከላከያ ሠራዊት በዘመናዊ መልኩ ጥቅምት 15 ቀን 1900 ዓ.ም የተመሰረተበትን ታሪክ በማሰብ ይከበራል።
ይህም ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የጦር ሚኒስትር የሰየመችበትን ቀን በማስታወስ ለሀገር ሉዓላዊነት መስዋዕትነት የከፈሉ ጀግኖች ይዘከሩበታል።
ዓላማውም የሠራዊቱን ጀግንነት፣ ሉዓላዊነት የማስጠበቅ ሚና እና ታላቅ አኩሪ ታሪክ ለትውልድ በቅብብሎሽ ማስተላለፍ ነው።
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ በዚሁ ወቅት እንዳሉት ዕድሜ ጠገብ ተቋማት ከገነቡ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ናት።
119 ዓመት ያስቆጠረው መከላከያ ቀዳሚው አንጋፋው ተቋም መሆኑንም ተናግረዋል።
የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሀገር አፍራሽ ባንዳዎችን እየተዋጋ መሆኑን ገልጸው፤ ሠራዊቱ የሀገር ህልውና ምሶሶ መሆኑን ገልጸዋል።
መላላክ የተጠናወተው ሕወሓት በለኮሰው እሳት መለብለቡን ገልጸው፤ ወደ ወዳጁ ሻዕቢያ ሄዷል ድጋሚም ዕድል እንደሌለው ተናግረዋል።
በተጨማሪም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ዓባይ የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ጸጋ ቀይ ባህርም ፈጣሪ ለኢትዮጵያ ያበጀው ባህር ነው ብለዋል።
የሀገር መከላከያ የቀጣናው አስተማማኝ ሀይል መሆኑን ገልጸዋል።
በመርሀ ግብሩ ሰራዊቱን በተለያዩ መንገዶች አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት የመከላከያ ሰራዊት የክብር አባልነት ተሰጥቷል።
@EthiopianNewsAgency
15 hours ago | [YT] | 384
View 10 replies
Ethiopian News Agency (ENA)
በ119ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን ለሠራዊቱ በተለያየ መንገድ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ዜጎች የመከላከያ ሠራዊት የክብር አባልነት እውቅና ተሰጠ
በ119ኛው የመከላከያ ሠራዊት ቀን ለሠራዊቱ በግላቸው በማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ የፈጠሩ እና በተለያዩ ሚድያዎችም ከሀገር ውጭም ጭምር ከሠራዊቱ ጎን በመቆም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ዜጎች የክብር የመከላከያ ሠራዊት አባልነት እውቅና ተሰጥቷል።
የክብር አባላቱ ከኢፌዴሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ እጅ የክብር የመከላከያ ሠራዊት አባልነት እውቅናቸውን ተቀብለዋል።
በዚህም፦
1. አቶ አፈወርቅ በደዊ ሀሰን
2. አቶ ቢኒያም ጌታቸው ወርቄ
3. አቶ ብሩክ አሰፋ በላይ
4. አቶ ዳዊት ካህሳይ ከለለ
5. ወ/ሪት ፍሬህይወት ይኋንስ ሶማ
6. ወ/ሮ ሂሪያ ዱፌራ በላቸው
7. አቶ ጃዋር አደም ኡመር
8. አቶ ምኡዝ ገ/ሂወት ወ/ስላሴ
9. አቶ ታዬ ቦጋለ አረጋ
10. አቶ ዮሀንስ ቢኒያም ዕ/ጽዮን
የክብር የመከላከያ ሠራዊት አባልነት እውቅናን ተቀብለዋል።
@EthiopianNewsAgency
16 hours ago | [YT] | 405
View 12 replies
Ethiopian News Agency (ENA)
ኢትዮጵያ ቀጣናውን በኤሌክትሪክ አቅርቦትና መሰረተ ልማት በማስተሳሰር ለሰላምና የጋራ ብልፅግና ቁርጠኝነቷን እያሳየች ነው
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናን በኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦትና በተለያዩ መሰረተ ልማቶች ለማስተሳሰር የምታደርገው ጥረት፣ ለቀጣናዊ ሰላም፣ መረጋጋትና የጋራ ብልፅግና ያላትን ፅኑ ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን የኢትዮጵያ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ።
"በአፍሪካ የሰላም መንገዶች የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የጅኦ ፖለቲካ ለውጥ" በሚል መሪ ሀሳብ በባህርዳር ሲካሄድ የቆየው 12ኛው የጣና ፎረም ዛሬ ፍፃሜውን ያገኛል።
በዛሬው እለት "የአፍሪካን የጅኦፓለቲካና ኢኮኖሚ መፃኢ ዕድል መቅረፅ" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ከፍተኛ ደረጃ የፓናል ውይይት ተደርጓል።
የኢትዮጵያ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የጣና ፎረም ለአፍሪካ ሰላም፣ ደህንነትና ልማት ወሳኝ አቅም ነው።
የአፍሪካ ሕብረት በዘንድሮው መድረክ የቀረበውን የጣና ፎረም በትኩረት በማየት ገቢራዊ ሊያደርገው እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።
በአፍሪካ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ በሀገራቱ መካከል ያለው ትብብር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል።
በአህጉሪቱ ጠንካራና ቀጣይነት ያለው ትብብር ለመፍጠር ጠንካራ የጅኦፖለቲካ አቅም መገንባት ይገባል ብለዋል።
የአህጉሪቱን ወሳኝ ማዕድናት የግጭት ሳይሆን የጋራ ልማትና ትብብር ማዕከል ማድረግ እንደሚገባም ገልጸዋል።
በሀገራት መካከል የተሟላ ትብብር መፍጠር ሳይቻል አህጉራዊ ግቦችን ማሳካት እንደማይቻልም አንስተዋል።
የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ትግበራ ያለበትን ውስንነት ለመቅረፍና የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ጥምረት ለማሳደግ የላቀ የፖለቲካ ቁርጠኝነትና የተሟላ የሀገራት ትብብር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ በቀጣናው ለተሰማራው የሰላም ተልዕኮ የላቀ ድጋፍ በማድረግ ለሰላምና ልማት ያላትን ጽኑ አቋም እያሳየች መሆኑን ተናግረዋል።
ሀገሪቱ ቀጣናውን በኃይል በማስተሳሰር በጋራ ለመበልፀግ በትብብር እየሰራች መሆኑንም አብራርተዋል።
የናይጀሪያ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጉድላክ ጆናታን በበኩላቸው፣ የአፍሪካን የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ዘመኑን የዋጀ የቴክኖሎጂ አቅም መገንባት እንደሚገባ ገልጸዋል።
የአፍሪካውያን የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የአፍሪካ መፃኢ ዕድል መወሰን እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
የተለያዩ የዓለም ሀገራት ከራሳቸው አቅምና ክህሎት በመነሳት የኢኮኖሚ ሉዓላዊነታቸውን እንዳረጋገጡ በማንሳት፣ አፍሪካም ይሄን አካሄድ መከተል እንዳለባት አንስተዋል።
የናሚቢያ ብሔራዊ ዕቅድ ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተር ካይሬ ምቡንዴ (ዶ/ር) ፤ ያለ ጠንካራ ሀገር፣ ያለ ጠንካራ አህጉራዊ ተቋማት ጠንካራ አፍሪካን መገንባት አይቻልም ብለዋል።
በአፍሪካ የኢንዱስትሪ አብዮትን በማቀጣጠል ሀብቷን ለሕዝብ ጥቅም ማዋል እንደሚገባም ገልጸዋል።
አፍሪካ በተፈጥሮ ሀብት የበለፀገች መሆኗን ገልጸው፤ የፋይናንስ ስርዓቱን በማዘመንና የሀገር ውስጥ የሀብት አሰባሰብን በመገንባት የውስጥ አቅምንና የገቢ ምንጮችን ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን አብራርተዋል።
@EthiopianNewsAgency
16 hours ago | [YT] | 149
View 0 replies
Ethiopian News Agency (ENA)
ጽምዶ የተባለው ሀይል በሰሜን ኢትዮጵያ የደረሰበትን ከባድ ሽንፈት ለመሸፈንና ትኩረት ለማስቀየር የብሔር እና የሃይማኖት ግጭት ለመፍጠር ያደረገው እንቅስቃሴ ከሽፏል - አቶ ሃይሉ አዱኛ
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 15/2019 (ኢዜአ)፦ ጽምዶ የተባለው ሀይል በሰሜን ኢትዮጵያ የደረሰበትን ከባድ ሽንፈት ለመሸፈንና የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር የብሔር እና የሃይማኖት ግጭት ለመፍጠር ያደረገው እንቅስቃሴ መክሸፉን የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ ገለጹ።
አቶ ሀይሉ አዱኛ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም ሀገራችን እያመጣች ያለውን እድገት በማስተጓጎል ሰላም እና ጸጥታን ለማናጋት የጠላት ኃይሎች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ፈጽሞ የማይሳካ መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ሃይሉ፤ እነዚህ የጥፋት ሀይሎች እየደረሰባቸው ባለው ከፍተኛ ሽንፈት የመንግሥትን የትኩረት አቅጣጫ ለማስቀየር እና የውስጥ ግጭቶችን ለማስፋፋት እየተፍጨረጨሩ መሆኑን ተናግረዋል።
የሸፍጥ እና የውድመት ሥራ ላይ የተሰማራው የጽንፈኛ ቡድን በደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ዞን በሰሸርካ ወረዳ በቾሌ እና ብርቦ ቀበሌዎች በንጹሐን ሕይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል ብለዋል።
በዚህም የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን እየገለጸ፤ እነዚህን አጥፊ አካላት ላይ ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን የጀመረውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አቶ ሃይሉ ገልጸዋል።
የክልሉ መንግሥት በዚህ ችግር ምክንያት ለተጎዱ እና ከቀዬአቸውና ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ከሕብረተሰቡ ጋር በመሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል።
@EthiopianNewsAgency
16 hours ago | [YT] | 46
View 15 replies
Ethiopian News Agency (ENA)
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና የአፍሪካ መሪዎች የባህርዳር ስታዲየምን ጎብኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት "12ኛውን የጣና ፎረም ከታደምን በኋላ፣ ከአፍሪካ መሪዎችና ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በመሆን ባሕር ዳር ስታዲየም ጎብኝተናል። ጉብኝቱ በስፖርት መሠረተ ልማት ረገድ ያለውን መሻሻል እንዲሁም ባሕር ዳር ለስፖርት፣ ለቱሪዝም እና ቀጠናዊ ትብብር ማዕከል የሚያደርጋትን ትልቅ አቅም ለመመስከር ዕድል የሚሰጥ ነበር" ብለዋል።
1 day ago (edited) | [YT] | 754
View 38 replies
Ethiopian News Agency (ENA)
"የሰላም መንገዶች በአፍሪካ፦ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና የጂኦፖለቲካ ሽግግር" በሚል መሪ ቃል በተካሄደው 12ኛው የጣና ከፍተኛ የደህንነት ፎረም ላይ ተገኝቼ ንግግር በማድረጌ ደስታ ተሰምቶኛል።
የጉባኤው መሪ ቃል ልንዘነጋው የማይገባንን እውነታ ያሳያል፤ ከድንበራችን ባሻገር የሚወሰኑ ውሳኔዎች በዜጎቻችን፣ በኢኮኖሚ ዕድሎቻችን እና በደህንነታችን ላይ ተፅዕኖ ያሳድራሉ። እያንዳንዱን ድንገተኛ ቀውስ መቆጣጠር ባንችልም፣ የመቋቋም አቅማችንን ግን ማጠናከር እንችላለን። ይህ ለአፍሪካ የሀገር በቀል መፍትሄዎችን ማዘጋጀት፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ማጠናከር እና ትብብርን ማሳደግ ማለት ነው። አፍሪካ እየተለወጠ ካለው ዓለም አቀፋዊ ሥርዓት ጋር መላመድ ብቻ ሳይሆን፣ ሥርዓቱን የመቅረጽም ሚና ሊኖራት ይገባል።
ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ቀዳሚና እጅግ አስፈላጊ ጉዳይ ነው። ይህም ዜጎችን መጠበቅ፣ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ማክበር እና ለውይይት በርን ክፍት ማድረግን ይጠይቃል። ለብሔራዊ ምክክር ባለን ቁርጠኝነት፣ የሰላምን መንገድ የሚመርጡትን ሁሉ ለመቀበል ሁልጊዜም ዝግጁ ነን።
የመደመር ፍልስፍና፣ ጥንካሬዎቻችንን እና አቅማችንን በማስተባበር እንዲሁም ከራሳችን ተጨባጭ እውነታዎች የተቀዱ መፍትሄዎችን በማዘጋጀት ላይ ያተኮረ መሆኑን ያስገነዝበናል። ለወደፊት ትውልዶቻችን የምናወርሳትን ዓለም ለመቅረጽ የላቀ ሚና እየተጫወትን፣ ጠንካራ የመቋቋም አቅም ያላት፣ ሰላማዊ እና የበለጸገች አህጉር መገንባት እንችላለን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
1 day ago | [YT] | 632
View 21 replies
Ethiopian News Agency (ENA)
"12ኛው ከፍተኛ የአፍሪካ ደህንነት ጉባኤ የሆነው ጣና ፎረም፣ የሰላም መንገዶች በአፍሪካ፦ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና የጂኦፖለቲካዊ ሽግግር፤ በሚል መሪ ቃል በይፋ ተጀምሯል። መድረኩ የአፍሪካ መሪዎችን እና ባለድርሻ አካላትን በማገናኘት በአህጉሪቱ ሰላም፣ ደህንነት፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እንዲሁም እየተቀያየረ ባለው ዓለም አቀፋዊ ሥርዓት ውስጥ አፍሪካ ስላላት ሚና ይመክራል" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
1 day ago | [YT] | 629
View 17 replies
Ethiopian News Agency (ENA)
"12ኛውና ከፍተኛ የአፍሪካ ደህንነት ጉባኤ የሆነው ጣና ፎረም ከመጀመሩ አስቀድሞ፣ የሞዛምቢኩን ፕሬዝዳንት ዳንኤል ቻፖን በደስታ ተቀብያለሁ። ትብብራችንን ማጠናከር እና የጋራ ጥቅሞችን ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያም የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል" ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
1 day ago (edited) | [YT] | 479
View 7 replies
Ethiopian News Agency (ENA)
12ኛውና ከፍተኛ የአፍሪካ ደህንነት ጉባኤ የሆነው ጣና ፎረም ከመጀመሩ አስቀድሞ፣ የኬንያውን ምክትል ፕሬዝዳንት ኪቱሬ ኪንዲኪን በመቀበሌ የተሰማኝን ደስታ ለመግለጽ እወዳለሁ፤ በጋራ ጉዳዮች ዙሪያም አጭር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
1 day ago | [YT] | 389
View 9 replies
Load more