በዚህ መንፈሳዊ የዩቲዩብ ቻናል ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሆኑ ማንኛውንም መንፈሳዊ ስብከቶች ፥ ዝማሬዎች እንዲሁም የተለያዩ መንፈሳዊ ፕሮግራሞች የሚለቀቅበት ቻናል ነው። አብራችሁን በመሆን ቻናሉንም ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተ ሰብ ይሁኑ።
————-
👉ይህን መንፈሳዊ ሚዲያ በገንዘብ ለመደገፍ የምትፈልጉ
Name : AbaTewelede Medehen Mekonen
CBE : 1000015066419
Abyssinia Bank : 52885302
አክሱም ጽዮን ሚዲያ | Axum Tsion Media
Axum Tsion Media አክሱም ጽዮን ሚዲያ
የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በዓለ ዕረፍት መጋቢት 5 ወይስ ጥቅምት 5 ? ጥቅምት 5 የሚከበርበት ምክንያት ዘርዝር/ሪ
በዚያን ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ይበራሉ። የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ።”
ማቴ 13 ፥ 43
እንኳን አደረሳችሁ !
ሊቀ ጉባኤ አባ ተወልደመድኅን መኮንን
5/2019 ዓ.ም
2 days ago | [YT] | 56
View 0 replies
Axum Tsion Media አክሱም ጽዮን ሚዲያ
እንኳን ለቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሃ በዓለ ዕረፍታቸው ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
#ያረፉበት ዓመተ ምሕረት
ንጉሥ አብርሃ በ374 ዓ.ም ጥቅምት 4
ንጉሥ አጽብሃ በ379 ዓ.ም ጥቅምት 4
የሁለቱ በዓለ ዕረፍታቸው በተመሳሳይ ቀን ነው።
ይህ በዓል በትግራይ ክልል በውቅሮ ክልተ አውላዕሎ አብርሃ ወአጽብሃ ገዳም ጥቅምት 4 በዓለ ዕረፍታቸው በድምቀት ይከበራል። የቅዱሳን አብርሃ ወአጽብሃ በረከትና ረድኤት ያድለን !
ሊቀ ጉባኤ አባ ተወልደመድኅን መኮንን
ጥቅምት 4/2019 ዓ.ም
3 days ago | [YT] | 53
View 0 replies
Axum Tsion Media አክሱም ጽዮን ሚዲያ
45ኛው አለም አቀፍ የሰበካ ጉባኤ ስነ ሥርዓት ጥቅምት 3/2019 ዓ.ም በጸሎት ተከፈተ
4 days ago | [YT] | 7
View 0 replies
Axum Tsion Media አክሱም ጽዮን ሚዲያ
ባእታ ለማርያም ጥቅምት 3
እመቤታችን ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ወርሐዊ በዓል ነው
እንኳን አደረሳችሁ።
5 days ago | [YT] | 55
View 1 reply
Axum Tsion Media አክሱም ጽዮን ሚዲያ
በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ግቢ የተገነባው ከ2260 በላይ ሰው መያዝ የሚችለው አዲሱ ዓለም አቀፍ መሰብሰቢያ አዳራሽ ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ጥቅምት 1/2019 ዓ/ም ሊመረቅ ነው።
1 week ago | [YT] | 9
View 0 replies
Axum Tsion Media አክሱም ጽዮን ሚዲያ
እምትካት አይሁድ በቅንአቶሙ ይጸልኡኪ ጥቀ
በእንተ ዘወለድኪ በድንግልና ወልደ ጻድቀ።
1 week ago | [YT] | 9
View 0 replies
Axum Tsion Media አክሱም ጽዮን ሚዲያ
#የአውሬነት ጥግ በሴት ልጅ ላይ እንዴት ይፈጸማል ?
👉የአክሱም ከተማ ተወላጅ የሆነችው ሮዛ ገ/ሚካኤል የጳጳስ ስም አጠፋሽ ብላችሁ በሳይክል እየሄደች ሳለች መስከረም 25 /01 /2019 ዓ.ም ጊዜ ጠብቃችሁ በመኪና ገጭታችሁ አካሏን ማጉደል ምን አይነት ነውረኝነት ነው በአክሱም ከተም ውስጥ የአክሱም ከተማና የአክሱማውያን ስም ለማጥፋት ሆን ተብሎ ሰይጣናዊና የረከሰ ሥራ እየተሰራ ነው ! አክሱማውያን ልትነቁ ይገባል አፍኒና ፍኒሐስ ከቤታችን አስወጡ።
👉ሮዛ በመኪና ከመገጨቷ በፊት ቪዲዮውን እንድታጠፋ በተደጋጋሚ የግድያ ሙከራና ዛቻ ይደርስባት እንደ ነበረ በራሷ አንደበት የገለጸች ቢሆንም በወቅቱ መፍትሂ ባለማግኘቷ ይባስ ብሎ እቅድ አቅዳችሁ ተከታትላችሁ በመኪና መግጨታችሁ እጅግ አሳፋሪ ድርጊት ነው።
👉ሮዛ ገብረ ሚካኤል በመኪና የገጯት ሰዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ሳይውሉ ከቦታው እንዳመለጡ እየተገለጸ ነው እሷ ግን እጅዋ ተሰብሮ ራሷ ላይም ተሰፍቶ ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶባት በአክሱም ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላት ይገኛል።
👉በግፍና በጭካኔ በመኪና ለተገጨች ለሮዛ ድጋፍና ድምጽ ልንሆናት ይገባል : ሰው ለማገዝ ሰው መሆን በቂ ነው።
👉ወንጀለኞ እና ወንጀለኞችን ገዝተው ያሰማሩ አካላት ለሕግ መቅረብ አለባቸው ዝሙትና ወንጀለኞቸእ ከአክሱም ምድር መወገድ አለባቸው።
👉ይህን ወንጀል ያስፈጸመው አካል ማን ይመስሏችኋል ?ሐሳባችሀኡን ኮሜንት ላይ አስቀምጡ።
#ፍትሕ በግፍ ለሚበደሉ እና ለሚገደሉ ሴቶች
ሊቀ ጉባኤ አባ ተወልደመድኅን መኮንን
መስከረም 29/01/2019 ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
1 week ago | [YT] | 3
View 0 replies
Axum Tsion Media አክሱም ጽዮን ሚዲያ
እንኳን ለብዙኃን ማርያም መስከረም 21 ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
ብዙኃን ማርያም ማለት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት መስከረም 21 ቀን የሚከበር ታላቅ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓል ስም ነው።
✔️ይህ ዕለት በሰፊው የሚታወሰው እና "ብዙኃን ማርያም" ተብሎ የተሰየመበት ዋና ዋና ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው:-
1ኛ. የኒቂያ ጉባኤ መታሰቢያ (ብዙኃን ሊቃውንት የተሰበሰቡበት)
በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አርዮስ የተባለ መናፍቅ “ወልድ ፍጡር ነው፤ ከእግዚአብሔር አብ ጋር አንድ ባህርይ አይደለም” በማለት የተሳሳተ ትምህርት በማስተማሩ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከፍተኛ ውዝግብ ተነስቶ ነበር።
በወቅቱ ጻድቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ባደረገው ጥሪ መሠረት 318 ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን (ብዙኃን ሊቃውንት) በኒቂያ ተሰበሰቡ።
✔️አርዮስን ለማውገዝ የተሰበሰቡት እና የክሕደት ትምህርቱን አውግዘው «እግዚአብሔር ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ከእግዚአብሔር አብ ጋር አንድ ባህርይ ነው (ማርያምም ወላዲተ አምላክ ናት)» ብለው የሃይማኖት ጽኑ መሠረት (ጸሎተ ሃይማኖት) የወሰኑት በእመቤታችን በዓል ዕለት (መስከረም 21) በመሆኑ፣ እንዲሁም ብዙኃን ሊቃውንት / ብዙ ሊቃውንት/ የተሰበሰቡበት በመሆኑ “ብዙኃን ማርያም” ተብሎ ይጠራል።
2ኛ. የግእዝ ቃል ትርጉም (እመ ብዙኃን)
“ማርያም” የሚለው ቃል በዕብራይስጥ ትርጉሙ “እመ ብዙኃን” ማለትም የብዙዎች እናት ማለት ነው።
(አብርሃም “አብ ብዙኃን” – የብዙዎች አባት እንደተባለ ሁሉ)። እርሷ ለዓለም ሁሉ ድኅነት የተገኘባት የሁሉ እናት መሆኗን ይታወቃል።
“ናሁ እምይእዜሰ ያስተበፅዑኒ ኩሉ ትውልድ”
እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል።
ሉቃ 1 ፥48
እኛ ልጆቿ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያ ሁሌ ብፅዕት፣ቅድሰእት ፣ክብርት፣ ልዕልት እንላታለን።
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ረድኤትና አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን!
youtube.com/@axumtsionmedia?si=IMBZ_6_iVhee2MFO
ሊቀ ጉባኤ አባ ተወልደመድኅን መኮንን
መስከረም 20/01/2019 ዓ.ም
2 weeks ago | [YT] | 119
View 2 replies
Axum Tsion Media አክሱም ጽዮን ሚዲያ
መስቀል አብርሃ በከዋክብት አሰርገወ ሰማየ
3 weeks ago | [YT] | 29
View 0 replies
Axum Tsion Media አክሱም ጽዮን ሚዲያ
የዶ/ር ሮዳስ ታደስ
መስከረም 10 ሥርዓተ ተክሊል ተፈጽሟል
3 weeks ago | [YT] | 483
View 3 replies
Load more